እኛ ማነን?

መልእክተ እንደናት ቻሪቴብል አሶሴሽን ፖሇቲካዊም ፣ ሐይማኖታዊም ያልሆነ ሇትርፍም ያልተቋቋመ ትኩረቱን በሴቶች ፣ በልጆች እና በወጣቶች ላይ አድርጎ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ማህበር ነው። የበጎ አድራጎት ማህበሩ በዋነኝነት የኢትዮጵያ ሴቶች ፣ ልጆች እና ወጣቶች ላይ የተጋረጡ የትምህርት ፣ የኢኮኖሚ ፣ የማሀበራዊ ፣ የጤና ፣ የስነ ተዋልዶ እና የመብት ችግሮችን እና ተግዲሮቶችን ሇመፍታት ተልእኮን ሰንቆ የተመሰረተ ማህበር ነው። መልእክተ እንዯናት ቻሪቴብል አሶሴሽን የተመሰረተው እውቀት እና ችሎታቸውን ሇትውልድ ሇማበርከት በሚፇልጉ ኢትዮጵያውያኖች ሲሆን በህዲር 2013 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ኤጀንሲ ህጋዊ ሰርተፍኬቱን ተቀብሎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ርእይ

የኢትዮጵያ ልጆች ፣ ሴቶች እና ወጣቶችን ብሩህ የወዯፊት ተስፋ እንዱኖራቸው እንዯናት መዯገፍ።

ተልእኮ

መንግስታዊም መንግስታዊም ካልሆኑ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ድርጅቶች ጋር በቅርበት እና በትብብር በመስራት የኢትዮጵያ ልጆችን ፣ ሴቶችን እና ወጣቶችን የህይወት ተግዲሮት እና ተጋላጭነትን በመቀነስ የመማር መብታቸውን ፣ የክህሎት እድገታቸውን ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እና የመሳተፍ እና መረጃ የማግኘት እና በአገልግሎት የመጠቀም መብቶቻቸውን ማረጋገጥ።